«

»

Mai 31

Beitrag drucken

43ኛው አጠቃላይ የህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ !!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

«ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።» ዕብ 13፥16

Holy-synod-43rd

ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሐዋርያት ተያይዞ የመጣውን በዓመት ሁለት ጊዜ የሚያካሂደውን የርክበ ካህናት የሆነውን ጉባኤ በዚሁ ዓመትም በሲያትል ክብረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተጋናጅነት ከግንቦት 17-19/2008 ዓ/ም ተካሂዷል። ጉባኤው በቤተክርስቲያናችንና በሀገራቸን ያለውን የወቅቱን መንፈሳዊና ማህበራዊ ችግሮች እና ሁኔታዎች የዳስሳና የመርመረ ጉባኤ ነበር ። ጉባኤው ከተጀመረበት እለት ጀምሮ መላው የጉባኤው አባላት ጠዋትና ማታ በጸሎት በመትጋት ፈቃደ እግዚኣብሔርን ጠይቆ በታላቅ መንፈሳዊነትና በትህትና ስሜት አካሂዷል ።

ጉባኤው በጥልቀት ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ሥርዓት መጠበቅ፣ እንዲሁም ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግሮች በሰፊው ተወያይቷል። በዚህ ዘመን ሐዋርያዊት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ኢትዮጵያ በትልቅ ፈተና ላይ መሆናቸው ያታወቃል። በዚህ ጊዜ ደግሞ ሁላችንም በጸሎት ልንተጋ በሐያማኖት ልንጸና ሀገራችንንም ተግተን በአንድነትና በፍቅር እንድትጸና በአድነት መሥራት ከሁሉም ይጠበቃል። ሀገራችንን በተመለከተ በአለው የአገሪቱ የመንግሥት አስተዳደር በፈጠርው ችግር ምክንያት በሀገራችን የተከሰተው ረሀብ በሕዝባቸን ያሰከተለውን መከራና ስቃይ በቂ ጊዜና ሰዓት ወስዶ ተወያይቶ ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ጉባኤው በአጠቃላይ መንፈሳዊ ማህበራዊ ሁኔታና ክስተቶችን መርምሮ ችግሮችን ነቅሶ ካወጣ በኋላ መፍቴዎቻቸውንም በማስቀመጥ ለተግባራዊነቱ የጊዜና የፍፃሜ ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔር በራሱ ጥበብ አንዲፈጸማቸው በጸሎት እየተማፀነ በታላቅ በረከት ከአጠናቀቀ በኋል በጋራ የሚከተለውን የአቅዋም መግለጫ አውቷል።

1) በስደት ላይ የሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እና ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቀጥል ሐዋርያዊ ተልዕኮ እንዲፋጠን፣ ትውልዱንም ከክፉው ዓለም ክፉ ሐሳብ እና ከኑፋቄ ለመጠበቅ፣ ምእመናንን በሃይማኖት ለማጽናት ተጨማሪ ኤጲስቆጶሳት በአፍሪካ፣ በአውሮጳ፣ በአውስትራልያ፣ በካናዳ እንዲሁም በዩናትድ ስቴትስም ባሉ አህጉረ ስብከቶች ሰኔ አስራ ሁለት ቀን 2008ዓ/ም / በበዓለጳራቅሊጦስ) እዲሰየሙ ወስኗል።

2) በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናን በሃይማኖት ጸንተው የውስጥ እና የውጭ የቤተ ክርስቲያንን ተግዳሮቶች በሃይማኖት እንዲጸኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል።

3). ቤተክርስቲያንን ለማሳደግ ለሀገር ለወገን የሚጠቅም የህሊናና የሞራል ብቃት ያለው ትወልድ ማፍራት እንዲቻል የሥነ ምግባርና የሰላም ሕበረተሰብ እንዲጠናክርና እንዲበረታ የጀርባ አጥንት በመሆን የሚያገለግለው ስብከተ ወንጌል መስፋፋት በመሆኑ ለዚህ የተጠሩ አገልጋይ ካህናትና መላው ምእመናን አንደነታቸውና ያላቸውን ግንኙነት በበለጠ በማጠናከር በመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሠራ ጉባኤ በአክብሮት ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በበለጠ ለመጠናከርና ለመሥራት ቃል ይገባል።

4). በሀገራችን ኢትዮጵያ መቸም ጊዜ ቢሆን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከሃያ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ እንዲራብ ከተፈጥሮው ችግር በላይ የጎሳው ቡድን በሚከተለው ቋንቋን መሠረት ያደረገ የአገዛዝ ስልት መሆኑ ነው። ከዚህም በላይ ለረሃብ ብቻ ሳይሆን ለበረሃ ስደት፡ ለባህር ስጥመት፡ ለጨካኞች ስለት የዳረጋቸው በመሆኑ ይህ ችግር ከምንጩ እንዲደርቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የየራሱን ድርሻ ከምንጊዜውም በላይ ያስፈለግበት ጊዜ ነው በተለይም ምሁራንና በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ድርጅቶ ከዚህ ግባ የማያብል ልዩነት እያሰፉ ከመሞት ይልቅ በአንድነት ተባብረው የአገር ማዳን ሥራቸውን ኃላፊነት ይወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ያደራ ጥሪ ያስተላልፋል።

5). በመንሥት ስም የተቀመጠው ቋንቋ ተኮር ፖለቲካ የሚያራምደው የመንግሥት አካል በሀገሪቱ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነ ከመሆኑ ባለፈ ለወንድማማቾች መገዳደልና አለመተማመን በቤተሰብ መካከል መበታተነን እያስከተለ ነው።

ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሰጡ የሃይማኖት አባቶችንም ጠልፎ ከመጣሉ ባሻገር ወደፊት በሀገሪቱ ላይ የለየለት የጎሳ ግጭት ቢከሰት ተው የሚል አካል ሊጠፋ እስከሚችል ድረስ ስጋት አሳድሯል። በመሆኑም ይህን ሀገርን አጥፊ ትውልድን ገዳይ አላማ ለማስቆም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲቃወምና እንዲያወግዝ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል።

6). አሁን በአገራቸን ያለው ጎሳ ተኮር ፖለቲካ የሚራምደው አካል እንደ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ የስልጣን ዘመኑን የሚያራዝምበትን ብቻ በመከተል ከበረሃ ጀምሮ ሲያራምደው በነበረው አንድ ለአምስት አደረጃጀት ሕዝብን የሚያሰጨንቅ አካል ነው። ስለዚህ ይህ አካል መኖሩን ሚያሳውቀው የራሱን ወገኖች ሲገል፡ ሲያስር፡ ሲያሳድድና ሲያንገላታ ነው። ይህ በመሆኑም ነው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ የሚኖሩ የራሱ ዜጎች በወጪ ወራሪ መገደላቸው እንዲሁም ህፃናትንና አረጋዊያንን ጨምሮ ቁጥራቸው በርካታ ዜጎቻችን ከነነፍሳቸው ታፍነው ሲወሰዱ ምንም አይነት የመከላከል እርምጃ አለመውሰዱ ለዜጎቹ ግዴሽነቱ ዓቢይ ማረጋገጫ ነው። ይህ አድራጎቱም ለማንኛያውም ኢትዮጵያውያን አሳዛኝና አስደንጋጭም ሆኖ ተግኝቷል ከዚህም የተነሣ የመንሥትነትን ሥልጣን ሊያሲዝ የሚያሰችል የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን ቅድስ ሲኖዶስ ያምናል።

7). በዚሁ ማህበረሰብ የተፈፀመው በውጭ ኃይል መደፈር ግድያና ታፍኖ መወሰድ አንገት አስደፍቶን በኃዘን ላይ እያለን ሕዝብን ለመግደልና ለማሰር የሚታጋው መንግስት ነኝ የሚለው አካል በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪ በተነሣው የመሬት መቀራመትን አሰመልክቶ በተቃወሙ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና በየ ክፍለ ግዛቶቹ በሚኖረው ማህበረሰብ ላይ እየፈጸመው ያለው የአፈና፡ የግድያና የአስራት አርምጃ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው የጭካኔ ሥራ ነው። በዚሁ የጫካኔ ሥራ ያለ አግባብ ፈሶ የሚጮኸው የንፁሀን ደም የፍትህ ጆሮ ሳያገኝ ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ቀጥሎ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ የሚተዳደርበትን የእርሻ መሬት ለመቀማት ሲል ለዘመናት ይዞት የነበረውን ማንነቱን ካልቀማሁ ብሏል ይኸው የገዥ ቡድን በየትኛውም ክፍል ውክልና ሳይኖረው በሌላው ማህበረሰብ ስም የማይፈልገውን ማንነት፡ ባህልና ቋንቋ በሃይል ለመጫን ያደረገውን ሃይል የተመላን እርምጃ የተቃወመውትን ከስምንት ሽ በላይ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ በደም አፍሳሽ ታጣቂዎቹ ከቦ በመያዝ በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ስለሆነም የሕዝባችንን መከራና ጭንቀቱን በመጋራት የሕዝቡ ጥያቄ ጥያቄችን ግፉ ግፋችን ስለሆነ የዓለም ሰላም ውዳድ ሕዝብ ከጎናችን እንዲቆምና አፋጣኝ የፍት ድምጹን እንዲያሰማ በታላቅ አክብሮት ጥሪ እናቀባለን።

8.) ከላይ የጠቀስናቸው በሕዝባችንና በሀገራችን ሞልተው እየፈሰሱ ያሉ የችግርና የመከራ ዓይነቶች በአግባቡ በመንግሥት ፖሊሲ ደረጃ እየተሠሩ መሆኑን በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የሰብዓዊ መብት ክፍል የወጡ ሪፖርቶች ምስክርነት ሰጥተዋል። እነዚህ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ የሚዘረዝሩ ሰነዶች ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩ ችግሮች የከፋ መከራ እንዳለ የሚያረጋግጡ መረጃዎችን የያዙ ሰነዶች ናቸው።

ስለዚህ ይህን መከራና ግፍ በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ኃይል መንግሥት ነው ብሎ መቀበል ለእኛ ለኢትዮጵያውን ቀርቶ ሰው ለሆነው ሁሉ ከባድ ሆኖ አግኝተነዋል በመሆኑ በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኢትያጵያን የሚወዱ ሁሉ ይህን ራሱ ሊያስተዳድረው ሊጠብቀው በሚችለው አገርና ሕዝብ ላይ ግፍን የሚፈጽም አመጸኛ አካል እንደ መንግሥት እንደይቀብሉ ቅዱስ ሲኖዶሱ እያሰገነዘበ በሞኝነትና በየዋህነት ተታለው ይህን አካል የሚደግፉ ጥቅም ተካፋዮች ሁሉ ከዚህ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡና ወደልባቸው ተመልሰው ንስሀ እንዲገቡ በደጋሜ ጥሪውን ያቀርባል ።

ነገር ግን ይህን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ሰምተው እያወቁ ከዚህ የግፍ መንግሥት ተብዬ ጋር ሕዝባችንን የሚበድሉ የግፍ ፖሊሲውን የሚያስፈጽሙ ለግፍ ማስፈጸሚያው በገንዘብ፡ በምክር በሞራል እርዳታ የሚያደርጉ ሁሉ እንዲሁም በንግድ ሽርክና የድሀውን ሕዝብ መሬት እየቀሙ የሚጠቀሙ እንዲሁም ንጹሀን ዜጎችን ለጥቅም ሲሉ እየወነጀሉ የሚያሳስሩ የሐሰት ወንጀል ለመፈጠር የስለላ ሥራ በምሥራት በወገኖቻችን ላይ ስቃይና ሰቆቃ እንዲፈጸምባቸው ሌት ተቀን የሚተጉ የግፈኞች አባሪና ተባባሪ ሆነው ጥቅምን የሚካፍሉ ጥቅምመኞች ከዚህ ግፈኛ መንግሥት ነኝ ባይ ጋር የተወገዙ መሆናቸውን ቅዱስ ሲኖዶሱ አጽኦት ሰጥቶበታል።

በመሆኑም በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ውግዘት በሥራ ላይ እንዲውል በማድረግ እረገድ እንድትተባበሩና ይህን ግፈኛ የጎሳ ቡድን በዜጎቹ ላይ የሚፈፅመውን አረመኔያዊ ተግባር በምትችሉት ሁሉ ለአለም ህብረተሰብ እንታሰሙ ቅዱስ ሲኖዶሱ አገራዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

9.) በአገራችን በኢትዮጵያ በህዝብ የተመረጠ መንግስትና መልካም አስተዳደር እንዲኖር የሚተጉ፡ እንደየትኛውም ዓለም የሰለጠነ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲኖር የሚጥሩ በፓርቲ ተድረጅተው የሚሥሩ ድርጅቶች፡ በዚሁ ጎሰኛ ቡድን የተፈፀሙ ግፎችንና የአስተድስደር ግድፈቶችን ያጋለጡ ጋዜጠኞች፡ ለሰው ልጆች ነፃነት የሚሰሩ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በአጠቃላይ ሰው ሲፈጠር ከአምላኩ የተሰጠውን መብት ነፃነት ተከብሮለት እንዲኖር የሚከራከሩ ምሁራን ሁሉ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የሚማቅቁባት ኢትዮጵያ አገራቸን ሰፊ አስር ቤት እንድትሆን አድርጓታል።

ከዚህም ባሻገር ይኸው ለግፍ የማይታክተው አገዛዝ እድሜው በረዘመ ቁጥር የሀገራችን የመከራ ጊዜ ስለሚቀጥል ይህ አካል ከዚህ በላይ በግፍ መቀጠል
የለበትም። በመሆኑም የሰላም የፍቅርና የመቻችል አገር እንድትሆንና ሕዝባችንም ሁሉም ከሚደርስብት ልዩ ልዩ መከራና ስቃይ ለመዳን በአንድነት እንዲነሣ ቅዱስ ሲኖዶስ ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

10). በሀገራችን የሰከነ የፖለቲካ ሥርዓት አለመኖር የፈፍጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ዜጎች በሀገራቸው እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው ሰርተው የመኖር እድልን የማይሰጥ በመሆኑ በዚህ መነሻነት ወደ ስደት በማምራት የፈለጉበት ቦታ ሳይደርሱ በአሲስ የተሰዉትን ሰማአታተ ኢትዮጵያ በሊብያ አመታዊ መታሰቢያቸውን ያደረገና ያዘከረ ሲሆን ይህ የክርስቲያኖችን መጨፍጨፍ አሁንም የቀጠለ ስለሆነ በቅርቡም በቦኮሐራም በናይጀሪያ ለትፈጁት ከሦስት መቶ በላይ ክርስቶያኖች ጸሎት አደርጓል፡፡ ሆኖም ይህ በክርስቲያኑ ማህበረሰብ ላይ የታወጀው የጀሀድ ጭፍጨፋ ያበቃ ዘንድ የአለም ማህበረሰብ ሁሉ በአንድነት እንዲነሳ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያደራ ጥሪውን ያስተላልፋል።

11). በሀገራችን በቅርቡ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን በፀሎት ያሰበ ሲሆን በአደጋው የአካልና የንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የበጎ ድራጎት ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጉላቸው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪውን ያስተላልፋል።

12). በቤተክስቲያናችን መሰደድ ምክንያት የተፈጠረው የሰላም እጦት ሁልጊዜም የቅዱስ ሲኖዶስ ጭንቀትና ሐሳብ ነው ። ምክንያቱም ከማንኛውም አገራችንን ከገጠማት ሁለንተናዊ ችግር ዋናው የቤተክርስቲያኒቱ መሰደድ ጉዳይ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው ይህ አገር አጥፊ ገዠ ቡድን መሆኑ ይታመንበታል ፡፡ ነገር ግን የተሰደደችው ቤተክርስቲያን ወደ አገር ተመልሳ የተጣሰው ቀኖና ወደ ነበረበት ቦታ ሲመለስና ቤተ ክርስቲያኒቱን ያሳደዳት ቡድን የሰላሙ እቅፋት ከመሆን ሲወገድ ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሁልጊዜ ለሰላም መሳካት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲደስር በመሆኑ አምላካዊ ፈቃዱ እንዲጨመረብት ሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን በጸሎትና በሐሳብ የየበኩሉን አስተዋጽኦ አንዲያደርግ በመጠየቅ በህጋዊው ቅዱሰ ሲኖዶስ በኩል ምን ጊዜም ቢሆን የሰላሙ በር ክፍት መሆኑን ያረጋግጣል።

በሐሳብ የየበኩሉን አስተዋጽኦ አንዲያደርግ በመጠየቅ በህጋዊው ቅዱሰ ሲኖዶስ በኩል ምን ጊዜም ቢሆን የሰላሙ በር ክፍት መሆኑን ያረጋግጣል።

13). ጉባኤው በጠቅላይ ቤተክህነት ስር የተቋቋሙ መምሪያዎች ያለባቸው ችግር ተቀርፎ ድርሻን ባለመቀማማት ሁሉን ያሳተፈና ቤተክርስቲያኒቱን ማዕከል ያደረገ ሥራ እንዲሰራ የሚመለከተው አካል ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ጥሪውን ያስተላልፋል።

ከዚህም ጋር አያይዞ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራችን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በየጊዜው የሚከሰተው ረሀብ እስራት ስደት ሞት ያበቃ ዘንድ በአገር ውስጥና በውጪ አለም የሚኖሩ ካህናትና ምእመናን በየአብያተ ክርስቲያናቱ አገራችንን ኢትዮጵያን እና የህዝቡን ስቃይ እያሰበ በፀሎት እንዲተጋ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

14). በመጨረሻም ይህ ታላቅ ጉባኤ ባማረና በሰመረ መልኩ ከአቀባበል ጀምሮ ሁሉን ያካተተ ፍቅርና ትህትና የተመላበት መስተንግዶ በማድረግ ጉባአኤው የተሳካ እንዲሆን ላደረጉት በሲያትል ለሚገኙ ምእመናን በተለይም ደግሞ ለክብረ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባላት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ምእመናን በሙሉ ይልቁንም የምዕመናንን አእምሮ በወንጌል በመማረክ ምእመናን ምን እናድርግ ምንስ አንታዘዝ አንዲሉ ያስተማሩና የመከሩ የደብሩን አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ ልዑለ ቃል አካሉን በማመስገን ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ::

ግንቦት 19 2008 ዓመተ ምህረት

ሲያትል ዋሽንግተን

 

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=606