Monatsarchiv: November 2014

Nov 25

ጾመ ነቢያት !!

“መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም።” ፩ቆሮ.፰፡፰ ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፡ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሰለጥንብኝም መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው” ብሏል። ‘አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ፡፡’’ ኢዩ.፪፡፲፪ ‘በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ፡፡ ጉባኤውንም አውጁ፡፡’’ ኢዩ.፪፡፲፭ ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=304

Nov 21

ኅዳር 12 በዓሉ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት!

በዚህ ዕለት የሚከበረው እስራኤልን ከምድረ ግብፅ እየመራ ማውጣቱን በማዘከር ነው፡፡ ይህስ እንደምን ነው? ቢሉ አብርሃም ይስሐቅን ይወልዳል፣ ይስሐቅ ያዕቆብን ይወልዳል፣ ያዕቆብ ይሁዳንና ዐሥራ አንድ ወንድሞቹን ወልዷል፡፡ ዐሥራ አንደኛው ዮሴፍ ነው፡፡ ወንድሞቹ ጠልተው ተመቅኝተው ለእስራኤላውያን በ20ብር ሸጡት እነዚህም ግብፅ ወስደው ለፈርዖን ቢትወደድ ለጲጥፋራ በ30 ብር ሸጡት 10 ዓመት በአገልግሎት 10 ዓመት በግዞት ቆይቷል፡፡ መተርጉመ ሕልም ነበር፡፡ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=302

Nov 21

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል!!

መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች‘ ተላላኪዎች‘ የእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ‘ የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡ ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ እግዚአብሔር‘ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?›› ማለት ነው፡፡ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.10፥13′ 2፥1/ ውስጥ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=299

Nov 21

“ዕፀ መስቀሉ ከየት መጣ”

“ዕፀ መስቀሉ ከየት መጣ” የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔ ኃይል ነውና እንደተባለው በቆሮ 1÷18/ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ መመኪያችን፣ ነፍሳችን መዳኛና የምንጸናበት መስቀል እናምናለን፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” እንዳለም /መዝ 131÷7/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ውሎ እኛ ለሠራነው ኃጢአት ካሣ እንደሆነ እያሰብን እንሰግድለታለን፡፡ በልባችን፣ በሰውነታችንና በቤታችን እንስለዋለን፡፡ በአባቶቻችን …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=296

Nov 21

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል…..ማር9:23

እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው … የአምስት ገበያ ያህል ሕዝብ ይከተለው ነበር በርካታ ሴቶችና ሕፃናት አረጋውያንና ወጣቶች፤ ከዚህ ሁሉ ሕዝብ መካከል እኩሉ ድውያንን ሲፈውስ እውራንን ሲያበራ በሚያደርገው ድንቅ የሆነ ተአምር ተከቦ እኩሉ መሲህ ይመጣል የተባለውን የሰማ እኩሉም በሚያስተምረው ትምህርት የተመሰጠ እኩሉም መልኩና ቁመናው የክርስቶስ ደም ግባቱ አስገርሟቸው ለማየት የሚከተሉ ነበሩ… ይህቺ ዓለም ተሸብራ የሰው ልጆች …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=291

Nov 21

ማዕተብ የክርስቲያን ዓርማ !!

„ማህተብህን በአንገትህ እሰረው ስትሔድ ይመራሃል ስትተኛ ይጠብቅሃል“ ምሳ 6÷21 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በአንገታቸው ላይ ክር ያስራሉ ለሕፃናቶቻቸውም ክርስትና ሲነሱ ክር ያስሩላቸዋል በሕፃናቱም ሆነ በአዋቂዎቹ ክርስቲያኖች የሚታሰረው ክር በግዕዝ ማዕተብ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቃሉ የወጣው ዐተበ ካለው ግዕዛዊ ግሥ ሲሆን ዐተበ ፍቺው አመለከተ ባረከ ማለት ነው፣ ማዕተብ ከዚህ ይወጣል ምልክት ማለት ነው፡፡ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች የክር ማዕተብ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=287

Nov 21

ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን !!

ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከክርስትና በፊት ሥዕል በቤተ አሕዛብም ሆነ በቤተ አይሁድ የታወቀና ከአምልኮት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ በቤተ አሕዛብ ዕንጨት ጠርቦ ደንጊያ አለዝቦ ማምለክ የተለመደ ነበር፡፡ እንዲያውም የሮማ ነገሥታት አማልክት ተብለው ከመመለካቸው በላይ ከሞቱ በኋላ ሥዕላቸው በደንጊያና በዕንጨት እየተቀረጸ ሲመለኩ መኖራቸው በታሪክ ይታወቃል፡፡ ክርስትና በመጣ ጊዜም ከክርስትና ጋር ያጣላቸው ይኸው ልማዳቸው ነው፡፡ በክርስትና …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=283

Nov 20

ጾም – ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው …ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ይኽን ጽሑፍ ወደ አማርኛ የመለስነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የኦሪት ዘልደትን መጽሐፍ ከተረጐመበት ከመዠመሪያው ድርሳኑ ላይ ነው፡፡ ስብከቱ ረዘም ስለሚልም አንዱን ድርሳን በክፍል በክፍል አድርገን አቅርበነዋል፡፡ ሊቁ ይኽን ስብከት የሰበከው ዐቢይ ጾም ሊገባ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት እንደኾነ ከስብከቱ መረዳት እንችላለን፡፡ ምንም እንኳን ከፊታችን የምንቀበለው ጾም ጾመ ነቢያት …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=280

Nov 20

ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ ….ደረጃ አንድ!!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ለዓለም ጀርባችንን እንስጥ እግዚአብሔር ለሰው እውቀትና ነጻ ፈቃድ ሰጥቶ አክብሮ ፈጠረው፡፡ አንዳንዶች ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው እውነተኛ የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆኑ፤ አንዳንዶች በስንፍናቸው ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ልግመኛ ክፉ አገልጋይ ሆኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ “እኔ ከየትኛው ነው የምመደበው? ከእውነተኞቹ አገልጋዮች ወይስ ከሀሰተኞቹ?” ብለን ራሳችንን እንጠይቅ ይለናል፡፡ የተጠመቀ ሁሉ የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሽ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=278

Nov 20

አብሬሽ ልመለስ !!

ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ከክብር ማረፊያው ከገሊላው ቤትሽ ሰማሁ መፍለስሽን ወደ ግብጽ ወደ ኩሽ ፀሐይ ሲያከትራት ያቺን የበረሃ ዖፍ ጼዋዌን ስትናፍቅ ላንዲት ቅጽበት ሳታርፍ ሰማሁኝ ስደቷን መጠጊያ ሳታገኝ በልቤ ላይ ስታልፍ ….ፈላሲተ ቁስቋም ወዴት ነው ሀገርዋ ኀበ ሖረት ላቲ በብካይ እትልዋ ናዛዚት እም ኃዘን ሁሉ ያላት ለማኝ የምድረ በዳ ዖፍ ጎጆዋን እስካገኝ መኃልየ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=273