Monatsarchiv: Oktober 2014

Okt 16

አብርሃ ወአጽብሐ !!

ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ/አህየዋ/ በቅድስና የሚኖሩ እግዚአብሔርን በቅድስና በንጽህና የሚያገለግሉ ነገር ግን ልጅ ያላገኙ መካኖች ነበሩ። ስለሆነም ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህ በትእዛዝህም የሚኖር ልጅ ስጠን እያሉ እግዚአብሔርን ይለምኑ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ስለ እግዚአብሔር ቸርነት ሲነጋገሩ ንግሥት ሶፍያ የሐና እመ ሳሙኤልን ጸሎት በመጥቀስ እሷም እንደ ሐና ሱባዔ ገብታ ፈጣሪዋን እንድትለምን ንጉሡን …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=269

Okt 13

ማሳሰብያ ስለ መምህር ግርማ ወንድሙ ወደ ሙኒክ መምጣትን አስመልክቶ

    ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ምዕመናን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ድረ ገጾች ላይ በቅርቡ በመንፈሳዊ አባትነታቸው የሚታወቁት መምህር ግርማ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ ጀርመን ሙኒክ ከተማ እንደሚመጡና ይህን ዝግጅት በሙኒክ የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስትያን አማካኝነት እንደሚካሄድ እየተነገረ ስለሆነና ብዙ ምዕመናንም ከተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=256

Okt 10

ማኅሌተ ጽጌ ክፍል አንድ !!

ማኅሌተ ጽጌ፤ ምንጩ ትርጉሙ መልእክቱ ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው፡፡ በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=245

Okt 06

አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ !!

ኢትዮዽያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ: እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነ…በሩ:: +ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በሁዋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን „ዮሐንስ“ አሉት:: በሒደት ግን …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=242

Okt 06

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን !!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ‹‹ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ›› 1ኛ ቆሮ 1፤23 ይህን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሮታል፡፡ የቀድሞ ስሙና ምግባሩ ሳውልና አሳዳጅ ማለት ነው፡፡ ሳውሎ ገማልያ ከተባለ ከኦሪት ሕግ አዋቂ ጠንቅቆ የተማረ ስለ ኦሪት ሕግና ስርአት አብዝቶ የሚጨነቅ ነበር፡፡በዚህ ምክንያት የክርስቲያኖች መብዛት የክርስቶስ አምላክነት በብዙ ቦታ ሲሰበክ እጅግ አብዝቶ ይጠላ ነበር፡፡በተለይ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=240

Okt 06

(ዘመነ ጽጌ) ነገረ ማርያም

„ልጄን ከግብፅ ጠራሁት“ (ት.ሆሴዕ 11፥1 ) አዘክሪ ድንግል ንግደቶ ዘምስሌኪ አንዘ ትጎይዩ ምስሌሁ እም ሃገር በመዋእለ ሄሮድስ ርጉም። አዘክሪ ድንግል አንብአ መሪረ ዘውኅዘ እማእይንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ። አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምአ ምንዳቤ ወሃዘነ ወኩሎ አጸባ ዘበጽሃኪ ምስሌሁ። ትርጉም፡- ድንግል ሆይ፤ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ከሃገር ወደ ሃገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋራ መሰደዱን …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=236

Okt 06

ቅድስት ዕሌኒ !!

የቅድስት ዕሌኒ ባለቤቷ ተርቢኖስ ይባላል፤ በቅድስና ተፋቅረው ነበር የሚኖሩት፤ ተርቢኖስ የሚል ጽሁፍ ያለበት የአንገት ሀብል አሰርቶላት ነበር። ተርቢኖስ ነጋዴ ስለነበር ከጓደኞቹ ጋር በመርከብ ተሳፍረው እሩቅ አገር ሄደው ከ 3 ዓመት በኃላ ይመለሳሉ ፤ ታዲያ መርከብ ላይ እንዲህ እያሉ ይጫወታሉ ፤ እኛስ በሰላም ወደ አገራችን ተመለስን ሚስቶቻችን ግን በሰላም ይጠብቁን ይሆን ሌላ ወንድ ወደውና ለምደው እንዳይጠብቁን …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=233

Okt 06

“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል” 1 ጢሞ. 6፣16

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከለት የመጀመሪያው መልእክት ማጠቃለያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስይህንን መልእክት ከአቴና በደቀ መዝሙሩ በቲቶ በኩል ልኮለታል፡፡ ይሄንን የመጀመሪያ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ በሔደጊዜ፤ ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስን በሃገረ ኤፌሶን ትቶት ሔዶ ነበር፡፡ በዚያ ቆይታው ስለ መንፈሳዊ አገልግሎቱና /እርሱም/ በመንፈሳዊሕይወቱ …

Weiterlesen »

Permanentlink zu diesem Beitrag: http://kidistmariammunich.de/wp1/?p=231